Blog

በኒያ ፋዉንዴሽን ዘሚ የኑስ ጆይ ኦቲዝም ማዕከል የPfizer ኮቪድ ክትባት ተሰጠ ህዳር 15፣ 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ..

በአገር አቀፍ ደረጃ  በዘመቻ በመሰጠት ላይ  የሚገኘው አራተኛው ዙር የኮቪድ ክትባት (የPfizer) በኒያ ፋዉንዴሽን  በዘሚ  የኑስ  ጆይ  ኦቲዝም  ማዕከል  ተሰጥቷል፡፡  በክትባቱም  ከ12  ዓመት በላይ የሆኑ የማዕከሉ  ተማሪዎች ፣ ቤተሰቦቻቸው  እና  የማዕከሉ ሠራተኞች  በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ዉዝጥ በመገኘት ክትባቱን  ወስደዋል፡፡

ከክትባቱ መርሐግብሩ  አስቀድሞ  የኮቪድ 19  ወረርሽን  እና  የክትባቱን  አጠቃላይ  ሁኔታ የሚዳስስ የግንዛቤ  ማስጨበጫ  ስልጠና  የተሰጠ  ሲሆን  በስልጠናው  የተማሪ ወላጆች  እና  የማዕከሉ ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡  የኮቪድ 19  ወረርሽኝ  አገራዊ  የስርጭት ሁኔታ፣ ኮቪድን  የመከላከል  እና የመቆጣጠር  ዋና  ዋና መንገዶችና መወሰድ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ፣  የኪቪድ ክትባትና  ኦቲዝም፣ ተዛማጅ የአዕምሮ እድገት ዉስንነት ጉዳይ፣ የክትባት ዓይነቶችና ጠቄሜታ ፣ ክትባቱን ለማግኘት  መሟላት ስለሚገባቸው  ቅድመ  ሁኔታዎችና  መሰል  ጉዳዮች  በኦሪዮንቴሽን  ገለፃው  ላይ  በትኩረት  ተዳስሰዋል፡፡

ገለፃውን  ያደረጉት  የወረዳ 04  ጤና  ፅ/ቤት  የበሽታዎች  መከላከል እና ቁጥጥር  የስራ ሂደት ኃላፊ አቶ  አብዲ አወል እንዳስገነዘቡት   ክትባቱን  የማግኘት  መብት የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መብት መሆኑን በማስመር ኦትዝም እና ተዛማች የአዕምሮ ዕድገት  ዉስንነት  እንዲሁም  ማናቸውም የአካል ጉዳት  ያለባቸው የህብረተሰብ  ክፍሎች የዚህ  መብት  አካል  በመሆናቸው  ተደራሽ  መሆን  ይገባቸዋል  ብለዋል፡፡  በዚህም መሰረት ዕድሜያቸው ከ12  በላይ እና 18 ዓመት በታች  ላሉ  ህፃናትና ወጣቶች  ወላጆች  ወይም የቅርብ ሞግዚት  ሀላፊነት  የሚወስዱበት  አሰራር  የተዘረጋ  በመሆኑ  ሙሉ  ፈቃደኝነታቸውን (Consent)  አስቀድሞ በማረጋገጥ የሚሰጥ  ክትባት መሆኑን አስረድተዋል፡፡   በገለፃው ላይ ከተሳታፊዎች በተነሱ ጥያቄዎች  ላይ  ምላሽና  ማብራሪያ  ተሰጥቷል፡፡

አቶ አብዲ አወል አያይዘውም  እንደገለጹት  የኮቪድ 19 ስርጭት  በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን  በመግለጽ  በአዲስ  አበባም ሆነ በክልሎች  በአሁን  ወቅት  የክትባት  ሽፋኑ   ከሚጠበቀው  አኳያ  እጅግ ዝቅተኛ  ደረጃ  ላይ  የሚገኝ  መሆኑን  በመጠቆም  በዚህ  ረገድ  የኒያ ፋዉንዴሽን  የዘሚ ጆይ  ኦቲዝም ማዕከል እንደ ተቋም የመከላከል ስራው ላይ ያሳየዉን ንቁ  ተሳትፎ  እንዲሁም  ከመጀመሪያው  የአስትራዜኒካ ኮቮድ ክትባት  ጀምሮ እስከ አሁን ባሉት የክትባት መርሃግበብሮች ላይ ተማሪዎችን፣ ሰራተኞችን  እንዲሁም  ቤተሰቦችን  በማስከተብ  ያሳየዉን  ንቁ  ተሳትፎ   በማድነቅ   ለተቋሙ  አመራሮችና ሰራተኞች  ምስጋናቸውን  አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም ተጨማሪ ሃላፊነት በመዉሰድ  ግንዛቤውን  በቤተሰብ  እንዲሁም  በማህበረሰብ  ደረጃ  ይበልጥ ለማስረጽ   በሚደረገው  ጥረት  ላይ   እንደ ተቋም  የበኩላችሁን   መወጣት  አለባችሁ ሲሉ ጥሪያቸውን  ከአደራ  ጭምር  አስታዉቀዋል፡፡

Share it on

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *